
ባሕር ዳር: የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምሕረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ የበጎ አድራጎት ድርጅት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስና መድኃኒቶች በአማራ ክልል ለሚገኙ 23 የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን ያስረከቡት የምሕረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ የበጎ አድራጎት ድርጅት ካንትሪ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሕይወት ወልዴ የተበረከተው ድጋፍ በአማራ ክልል ለሚገኙ 23 የጤና ተቋማት የሚውል መኾኑን አስረድተዋል። ድርጅቱ የጤና ተቋማቱን ሊደግፍ የሚችል 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስና መድኃኒቶችን ማበርከቱን ነው የተናገሩት።
ከአሁን በፊትም ድጋፍ ማድረጋቸውን ያስታወሱት ካንትሪ ዳይሬክተሯ ወደፊትም ቢኾን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘበናይ ቢተው ድርጅቱ ያበረከተው የሕክምና መድኃኒቶችና ቁሳቁስ በተለይ በጦርነቱ ለተጎዱ የጤና ተቋማትን በማገዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከድርጅቱ የተገኘውን ድጋፍ ለጤና ተቋማቱ እንደሚያከፋፍሉም ገልጸዋል። ለተበረከተው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ዘበናይ ሌሎች ተቋማትም መሰል ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
