
እንጅባራ: የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተውጣጡ ወጣቶች በትግል ወቅት ድምፅ በመሆንና በተግባር በመታገል አጋርነቱን ላሳየው የአዊ ሕዝብ ምስጋና ለማቅረብና የባህልና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አድርገዋል፡፡ ወጣቶቹ እንጅባራ ከተማ ሲደርሱም በአገው ፈረሰኞች ማኅበር፣ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በከተማው ነዋሪዎችና በመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ አማራዊ ማንነትን በኃይል ለመንጠቅ ባደረገው ትንቅንቅ በሕዝቡ ላይ ተነግረው የማያልቁ በርካታ በደሎች መፈፀማቸውን ወጣቶቹ ከእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ወጣት መርከብ ሰርብ ጉብኝቱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከዘመናት የግፍ አገዛዝ ነፃ እንዲወጣ መስዋእትነት ለከፈሉና ድጋፍ ለሰጡ የአዊ ወንድምና እህቶች ምስጋና አቅርቧል፡፡
በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ይርጋ ወሌ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በኃይል ከተጫነበት ማንነት እንዲላቀቅ በተደረገው ትግል የብሔረሰብ አስተዳደሩ ወጣቶች የሕይወትና የአካል መስዋእትነት ከፍለዋል ብለዋል፡፡
ብሔረሰብ አስተዳደሩ ለዞኑ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ሳሙኤል አማረ-ከእንጅባራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
