በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ኤርትራዊያን ስደተኞች ተናገሩ፡፡

164

ደባርቅ: የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ማይጠብሪ አካባቢ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የቆዩ እና በሚደርስባቸው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ወደ ደባርቅ ከተማ የተፈናቀሉት ስደተኞች አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽምባቸው መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን ማይጠብሪ ከተማ አሥተዳደር በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በርካታ ኤርትራዊያን ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ስደተኞቹ ከሚኖሩበት መጠለያ ጣቢያ በአሸባሪ ቡድኑ በየጊዜው እየተፈናቀሉ ሲሆን የሰሜን ጎንደር ዞን አሥተዳደር የሚፈናቀሉትን ስደተኞች እየተቀበለ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ እንዲቆዩ አድርጓል፡፡
ስደተኞቹ እንደተናገሩት አሁን ላይ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ሕዝብ እያደረሰ ካለው ግፍ ባለፈ በመጠለያ ጣቢያ በሚኖሩት ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይም ከፍተኛ በደል እየፈጸመ ነው ብለዋል፡፡
ከማይጠብሪ አካባቢ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የተፈናቀለው ወጣት መርሃዊ አብርሃ “እኛ በረሃ አቆራርጠንና በጨለማ ተጉዘን ወገን ካለበት መድረስ ብንችልም ብዙ ወገኖቻችን በትግራይ ወራሪ ቡድን መንገድ ላይ ተገድለውብናል፤ በመድኃኒት፣ በምግብና በውኃ እጦት ብዙዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው፤ የሚመለከተው አካል በመጠለያ ላሉት ወገኖች ይድረስላቸው፤ ይህን ዓለም ማወቅ አለበት፤ አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጥ” ብሏል፡፡
ወጣት መርሃዊ ከሞት ተርፈን ወገን ካለበት በመድረሳችን እንደገና የተወለድን ያህል ተሰምቶናል ነው ያለው፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የደባርቅ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ንዋይ መንግሥቱ የዳባት ማኅበረሰብ ዓለምዋጭ በተባለ ቀበሌ ለስደተኞች መጠለያ እንዲሠራ 91 ሄክታር መሬት ማስረከቡን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ሰኔ 26/2013 ዓ.ም በ 8 ሄክታር መሬት ላይ 25 ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የመጠለያ ጣቢያ ግንባታ ተጀምሮ ከ 7 ወር በኋላ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ ተፈናቅለው የመጡ እና በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ 1 ሺህ 400 ኤርትራዊያኖች ወደተዘጋጀው ቋሚ የስደተኞች መጠለያ እንዲገቡ ተደርጓልም ብለዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤን ኤች ሲ አር) የጎንደር ዋና ኀላፊ ማማዱ ላሚን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ሥራ ከማኅበረሰቡ ትብብር ውጭ የሚታሰብ እንዳልነበር ተናግረው ኅብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለስደተኞች መሠረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላት፤ ስደተኞቹ ከማኅበረሰቡ ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማስቻል የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ ያለዓለም ፈንታሁን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ በርካታ ኤርትራዊያን በየጊዜው እየተፈናቀሉ ወደዞኑ ከተሞች ሲመጡ የፀጥታ ኀይሉና ማኅበረሰቡ በእንክብካቤ እየተቀበለ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ እንዲቆዩ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡-አድኖ ማርቆስ-ከደባርቅ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፈፅመዋል የተባለው ወንጀል አሳስቦኛል” አሜሪካ
Next articleከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተውጣጡ ወጣቶች በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡