
ባሕር ዳር: የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸው መገለጹ በእጅጉ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በተመለከተ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የህወሓት ታጣቂዎች በ2013 ዓ.ም ነሐሴ ወር መጨረሻ እና በ2014 ዓ.ም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ በአማራ ክልል አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደፈፀሙ መግለጹን አስታውሷል።
ሁሉም ወገኖች በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቆም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል።
ግጭቱን ለማስቆም እና ለሁሉም ተበዳዮች ፍትሕን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል ቃል አቀባዩ።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
