
የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ማን ነህ? ሲባል አማራ ነኝ ለማለት ዛሬ ሳይኾን በዚያ የግፍ ዘመን እንኳን አልፈራም፡፡ ብዙዎቹ ስለማንነታቸው ሲሉ ከሽብር ቡድኑ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው እና ተዋግተው እስከወዲያኛው አልፈዋል፡፡ የአካል ጉዳት እና መፈናቀል፣ ስደት እና ግርፋት፣ መከራ እና ግፍ አማራ ነን ስላሉ ብቻ ያስተናገዱት ወልቃይቴዎች ዛሬ ላይ በሕዝብ መራር ትግል ባገኙት ነጻነት ከአማራ ወንድሞቻቸው ጋር በአንድ ተሰባስበው የሚመክሩበት እድል አግኝተዋል፡፡
በባሕር ዳር ተገኝተው ከጎናቸው ለነበሩ ወገኖቻቸው ኹሉ “ወደ እውነተኛ ማንነታችን እንድንመለስ እስከ ሕይዎት መስዋእትነት የደረሰ ዋጋ ስለከፈላችሁልን እናመሰግናለን” ያሉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች ለዘመናት ተጭኖብን ከነበረው የተውሶ ማንነት በትግላችን አሸንፈናል፤ አሁን ላይም በእውነተኛ ማንነታችን ተደራጅተናል፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡


ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ በግፈኛው አገዛዝ ምክንያት ከእውነተኛ ማንነቱ ርቆ በተውሶ ማንነት ውስጥ እንዲኖር ተገድዷል ያለን ወጣት ቃኘው መኮንን የተውሶ ማንነቱ በሕዝቡ ላይ ያሳደረው ሥነ ልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ብሏል፡፡ ወጣቱ ትውልድ እውነተኛ ማንነቱን እንዲያውቅ እና በማንነቱም እንዲደምቅ የአማራን ሰፊ ባሕል እና እሴት የሚያውቅበት አውድ መፈጠር ይኖርበታል ብሏል፡፡
ባለፉት ዓመታት የአማራ ሕዝብ ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ከጭቆና ቀንበር ነጻ መውጣት ወድ መስዋእትነት ከፍሏል ያለን ደግሞ ወጣት አየነው መንግሥቱ ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ በአራቱም አቅጣጫ “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እያለ በህቡዕና በአደባባይ ታግሏል ያለው ወጣቱ ስላለፈው አመስግኖ ስለመጭው መምከር እና በሚገባ መተዋወቅ ያስፈልጋል ነው ያለው፡፡ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ኹሉም ወጣቶች ሊጎበኙ ይገባል ብሏል፡፡
በቋንቋችን እንዳንናገር፣ በባሕላችን እንዳንደምቅ እና በማንነታችን እንዳንኮራ ተደርገን ቆይተናል፤ አሁን ላይ ግን እውነተኛ የአማራ ማንነታችንን እያጣጣምን ነው ያለችን ደግሞ ወይዘሮ ተሾመ ናት፡፡ እንደ እርሷ ኹሉ ሌሎች እህት ወንድሞቿም በቀጣይ የክልላቸውን አካባቢዎች እንዲያዩ እድል ሊፈጠርላቸው ይገባል ነው ያለችው፡፡
ወጣቶቹ በቀጣይም የተለያዩ አካባቢዎችን በመዘዋወር እንደሚጎበኙ ከመርኃ ግብሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
