የወልቃይት ወጣቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት አሸባሪውን ትህነግ ከሥሩ ለመንቀል ከወገናቸው ጋር ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ገለጹ።

216

ጎንደር: የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች በጎንደር ከተማ ትናንት ጉብኝት አካሂደዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ በርካታ በደሎችን አድርሷል። ማንነትን መሠረት ያደረገ የከፋ ግፍ ደግሞ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች ላይ ፈጽሟል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሐመራ ዞን
አማራዎች በአሸባሪው ትህነግ የጭቆና አገዛዝ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮም የሚደርስባቸውን ግድያ፣ አካላዊ ጥቃት፣ የማንነት ረገጣ፣ የሐብት ዘረፋና መፈናቀል ለማስቆም ጫካ ወጥተው አምርረው ታግለዋል።

ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎም ከአሸባሪው የትግራይ ቡድን በአሁኑ ወቅት ነፃ በመውጣት ወልቃይቴዎች በራሳቸው ባህልና ማንነት መኖር ጀምረዋል። በራሳቸው ቋንቋ መማርና መናገር ችለዋል፤ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትንም ከቅድመ አያቶቻቸው በወረሱት ወግና ባህል እያከበሩ ነው።

በአሸባሪው የትግራይ ቡድን ግፍ ለሦስት አስርት ዓመታት ማንነታቸው ከፈለቀበት ከአማራ ሕዝብ ጋር ተነጥለው የቆዩት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ወጣቶች በዚህ ወቅት የወንድምና እህቶቻቸውን ፍቅር ማጣጣም ጀምረዋል።

ወጣቶቹ ትላንት ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታም አሸባሪ ቡድኑ ሲያደርስ በነበረው ግፍ በሺዎች የሚቆጠሩ አባት፣ እናት፣ ወንድምና እህቶቻቸው ደብዛቸው እንደጠፋ ገልጸዋል።
ይህን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ከሥሩ ለመንቀል ከወገናቸው ጋር ሆነው ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በወላጆቻቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ስለጎንደር ከተማና ወገን ሕዝባቸው ሲነገራቸው የነበረውን ባሕልና ማንነት በአካል ተገኝተው በመመልከታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ወጣቶች በጎንደር፣ በባሕር ዳርና ሌሎች ከተሞች እያደረጉት ያለው ጉብኝት የወልቃይት ሕዝብ ነፃ እንዲወጣ መላው የአማራ ሕዝብ ላደረገው ተጋድሎ ለማመስገን፣ የእርስ በእርስ ግኑኝነትን ለማጠናከር፣ የቆየውን የአባቶቻቸውን ባህልና ማንነት ከወገናቸው ጋር ለማሳደግ፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን ለማጠናከር መሆኑን የዞኑ ወጣቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መራከብ ሰርብ አስገንዝቧል።

ከሰሜን ሽዋ እስከ ወሎ ያሉት አካባቢዎች የጉብኝቱ አካል መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የአማራ ሕዝብ በአሸባሪው ትህነግ አገዛዝ ሲደርስበት የነበረውን ግፍ በመቃወምና በመታገል ወጣቶች መስዋእትነት መክፈላቸውን የአማራ ክልል ብልጽግና ወጣቶች ሊግ ኀላፊ አቶ ጋሻው ተቀባ ተናግረዋል።
የአማራ ሕዝብ አንድነቱ ተጠናክሮ ጠላቶቹን ማጥፋት እንዲችል የወጣቶች ኀላፊነት ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ:–ዳንኤል ወርቄ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የአማራ ሕዝብ ትግል እንደ እንጉዳይ ነው” አቶ አሸተ ደምለው
Next article❝ወጣቱ ትውልድ እውነተኛ ማንነቱን እንዲያውቅ እና በማንነቱም እንዲደምቅ የአማራን ሰፊ ባሕል እና እሴት የሚያውቅበት አውድ መፈጠር ይኖርበታል❞ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች