“የአማራ ሕዝብ ትግል እንደ እንጉዳይ ነው” አቶ አሸተ ደምለው

214

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወጣቶች ልዑክ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ምሥጋና እያቀረቡ ነው፡፡ ትናንት ጎንደር የነበሩት ወጣቶቹ ዛሬ ደግሞ በክልሉ መዲና ባሕር ዳር ደርሰዋል፡፡

ላለፈው ምሥጋናን ለመጭው ትብብርን እና በአንድነት መቆምን ዓላማ ያደረገው የወጣቶቹ ጉብኝት ረፋዱ ላይ ተጀምሯል፡፡ የፖለቲካ ሴራ፣ የሹመኞች ሸፍጥ፣ የአምባገነኖች ግድያ እና አፈና እውነተኛ ማንነትን ይፈትነው ይኾናል እንጂ ፈጽሞ እንደማያጠፋው ከዓለም ታሪክ አይተናል ያሉት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) እንግዶቹን እንኳን ደኅና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡

ዛሬ የቆማችሁባት ከተማ በአማራ ሕዝብ የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ በማይረሳው መልኩ በአንድ ቀን ብቻ ከ50 በላይ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈውባታል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የሕይዎት መስዋእትነት የከፈሉት ወጣቶች መሳሪያ ያነገቡ ሳይኾኑ “ወልቃይት ኾይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” የሚል መልዕክት የያዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ነበሩ ብለዋል፡፡

እንደ ወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ኹሉ በየአካባቢው ያለው የአማራ ሕዝብ መራር መስዋእትነትን ከፍሎ በመጨረሻም አምባገነኖችን እስከ ወዲያኛው አባሮ ነፃ ወጥቷል ያሉት ዶክተር ድረስ ትግሉ ተገባደደ እንጂ አልተጠናቀቀምና በቀጣይም በአንድ ቆመን የጋራ ጠላታችንን መቅበር ይኖርብናል ብለዋል፡፡ የጉብኝቱ እና የውይይቱ ዓላማም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆም ነው ብለዋል ዶክተር ድረስ፡፡

ከሁለት ሀገራት አዋሳኝ፣ ከአማራ ምድር ተፈጥሯዊ ወሰን ተከዜ እና ከበርሃዋ ገነት ወልቃይት ጠገዴ ተነስተው በጣናዋ ፈርጥ ውቢቷ ባሕር ዳር የገቡት ወንድሞቻችሁ ዓላማቸው ስለትናንቱ መስዋእትነታችሁ ምሥጋና ለማቅረብ ነው ያሉት ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አሸተ ደምለው ናቸው፡፡ ወልቃይትን በአካል ሳታዩ “ወልቃይት ኾይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” ብላችሁ ለከፈላችሁት የአካል እና የሕይዎት መስዋእትነት ደግመን እና ደጋግመን ልናመሰግናችሁ እንወዳለን ነው ያሉት፡፡

“የአማራ ሕዝብ ትግል እንደ እንጉዳይ ነው” ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ቀን ሲጥለው የጠፋ፣ የደበዘዘ እና የተረሳ ቢመስልም ፈጽሞ የማይከስም ነውና ከመራር መስዋእትነት ወደ ቀደመ ርስቱ እና ማንነቱ ከተመለሰ አንድ ዓመት አልፎታል ብለዋል፡፡ ትግሉ አሁንም ፈተናዎች ቢኖሩትም ካለፈው ስለማይበረታ ያለጥርጥር እናሸንፋለንም ነው ያሉት፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከአማራዊ ማንነቱ በኃይል ተለይቶ በቆየባቸው ዓመታት ከስድስት በላይ ጀምላ መቃብር የሚገኝበት፣ ሰው ከነሕይዎቱ የተቀበረበት እና ትውልዱ ሊጠፋ ዳር የደረሰበት ነበር ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህ ኹሉ ኾኖ ግን ከአማራዊ ማንነታችን መነጣጠል አልቻለም ብለዋል፡፡

“ከአማራ መለየት አንችልም ምክንያቱም በበጌምድር ስሜን ጠቅላይ ግዛት ወገራ አውራጃ የምንኖር አማሮች እንደነበርን አባቶቻችን ነግረውናል” ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም አሸባሪው ትህነግ ዳግም ወደ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከመጣ አትጠራጠሩ መቀበሪያው በዚያ ይኾናል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዋጋ ግሽበት እና ለኑሮ ውድነት ጥያቄው ምን ምላሽ ሰጡ?
Next articleየወልቃይት ወጣቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት አሸባሪውን ትህነግ ከሥሩ ለመንቀል ከወገናቸው ጋር ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ገለጹ።