‹‹የጎርጎራ ልማት ፕሮጀክት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል፤ መስከረም/2015 ዓ.ም ላይ ሥራ ስለሚጀምር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

249

የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በምክር ቤት አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥኩረቱን ባደረገው ማብራሪያቸው የሀገሪቱ ቱሪዝም በኮረና ቫይረስ እና በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ጫና እንደደረሰበት አስታውቀዋል፡፡ ሆኖም ግን የቱሪዝም መዳረሻ ግንባታ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ሲሠራ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

‹‹ጎርጎራ ላይ የተጀመረው ልማት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል፤ መስከረም ላይ ሥራ ስለሚጀምር ተጋብዛችኋል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር ዐቢይ እንዳሉት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ጎርጎራ ላይ የተሠራው ሥራ ለኢትዮጵያውያን እና ለየትኛውም ዓለም ጎብኝ የሚመጥን ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት የጭቅጭቅ መንስዔ የሆነውን የዓባይ ተፋሰስ ምንጭ የሚያሳይ ብዙዎች የማያውቁትን ዓባይን በቅርበት እንዲመለከቱትም ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡ ይህም እጅግ ተስፋ የተጣለበት ትልቅ ፕሮጀክት እንደሆነ ነው ያስታወቁት፡፡

የኮይሻ ፕሮጀክትም በዚሕ ዓመት ይጠናቀቃል የተባለው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ነው፡፡ የዚህ አካል የሆነው የወንጪ ፕሮጀክት ግን ፈተና እንደገጠመው ነው ያስረዱት፡፡ ያጋጠሙትን ችግሮች በመፍታት በፍጥነት ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የአብያታና ሻላ አካባቢ ትልቅ አቅም መሆኑን በማንሳትም ማልማት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ከተማ መገንባት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ የተጀመረውን ማጠናቀቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ያሉ የተፈጥሮ ጸጋዎችን ማልማት የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት እንደሆነም ለምክር ቤት አባላቱ አስገንዝበዋል፡፡

በተያዘው ዓመት የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲነቃቃ መደረጉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት ያደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የገቡ የዳያስፖራ አባላት የቱሪዝም ዘርፉን በከፍተኛ ደረጃ እንዳነቃቁት አመላክተዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ በጂኦ ፖለቲካ ዘርፉ እና በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደነበራቸው ነው ያመላከቱት፡፡

ኢትዮጵያ ሰላም መሆኗንና የተረጋጋች ሀገር መሆኗን በማሳወቅ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ደጀኔ በቀለ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleባለፉት ስድስት ወራት አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከውጭ ሊገባ የነበረ ምርት በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡
Next articleጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዋጋ ግሽበት እና ለኑሮ ውድነት ጥያቄው ምን ምላሽ ሰጡ?