
የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በተከሰተው ጦርነት፣ በድርቅ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የኢኮኖሚ ቀውስ ተከስቷል፡፡ የኑሮ ውድነት ማስከተሉንም ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጅ ችግሮችም ቢኖሩ መልካም ዕድሎችን በመጠቀም የተሻሉ ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም በስድስት ወሩ 185 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የእቅዱን 92 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጸጸር 15 በመቶ እድገት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
በስድስት ወሩ የተሻለ ገቢ አሰባሰብ ቢታይም በሀገሪቱ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከባለፈው ዓመት ከወጣው ወጭ በ39 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የበጀት ጉድለት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ሰፋፊ የማክሮ ኢኮኖሚ እርማት ሥራዎችን ማከናወን ካልተቻለ የኢኮኖሚ ጉዞውን አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል አንስተዋል፡፡ ለዚህም ወጭ መቀነስ የሚያስችል ሥርዓት መከተልን እንደ መፍትሔ አስቀምጠዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት የሀገሪቱ የወጭ እና ገቢ ንግድ በተመሳሳይ 25 በመቶ ማደጉን አመላክተዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ባለፉት ስድስት ወራት ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶችን ለማሰቀረት ከፍተኛ ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡ በዚህም አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከውጭ ሊገባ የነበረ ምርት በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን ምርት በሀገር ውስጥ በመተካት እና ወደ ውጭ የሚላክን ምርት በማሳደግ የተስተካከለ የንግድ ሚዛን መፍጠር እና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ መሥራት ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ የፋይናንስ ዘርፉም ለጦርነቱ እና ለድርቁም ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡ ይህም ኾኖ የባንኮች አጠቃላይ ሀብት ከነበረው 1 ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር በስድስት ወሩ ወደ 2 ትሪሊዮን ብር ማደጉ ተነስቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ የ‹‹ሼር ሆልደሮች›› ሀብት ከነበረው 150 ቢሊዮን ብር ወደ 159 ቢሊዮን ብር ወይንም 7 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል፡፡ የባንክ ቅርንጫፎችም በስድስት ወሩ መጨመሩን ገልጸዋል፡፡
በሀገሪቱ ከነበረው 1 ነጥብ 35 ትሪሊዮን ብር ተቀማጭ ሀብት ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ማደጉን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም ቁጠባ ላይ መሥራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ለግብርና፣ ለአገልግሎት፣ ኢንዱስትሪ ዘርፎች 147 ቢሊዮን ብር ለብድር ወጭ እንደኾነም ተገልጿል፡፡ በዚህም ለግብርና ሴክተር የሚደረገው ብድር ዝቅተኛ በመኾኑ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ለግል ሴክተሩ የሚሰጠው ብድርም 69 በመቶ መድረሱ ተነስቷል፡፡ በቀጣይም ለግል የሚሰጠው የብድር አገልግሎት ማደግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
