
የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ሱዳን ጁባ ነዋሪ እና የጄቲኤን አጠቃላይ የንግድና ኢንቨስትመንት ባለቤት ኢንጂነር ታደሰ ኦልጅራ በጁባ የኢፌዴሪ ኤምባሲ በመገኘት የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያውን ዙር የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ በመካሄዱ ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን በመግለጽ በቤተሰባቸው ስም የ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።
በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ኢንጂነሩ በደቡብ ሱዳን በተለያዩ የንግድና የኮንስትራክሽን መስኮች ላይ በመሠማራት ለሀገሪቱ ልማት ብሎም ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የበኩላቸውን ድርሻ በመወጣት ላይ በመሆናቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በሀገር ቤት ለሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎችም ተከታታይ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ኢንጅነሩ ለህዳሴ ግድብና ለሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ኢንጅነር ታደሰ ኦልጅራ ካሁን በፊት ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለሌሎችም ጉዳዮች ካደረጓቸው ድጋፎች በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ጥር ላይ የ20 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ የፈጸሙ መኾኑን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
