
አዲስ አበባ: የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ዓድዋስ” የተሰኜ ትያትር የፊታችን የካቲት 22 በወዳጅነት አደባባይ ለዕይታ እንደሚበቃ ተገለጸ።
ስለትያትሩ መግለጫ ተሰጥቷል።
126ኛው የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ እንደኾነ የተነገረው ትያትሩ የካቲት 22 ምሽት 12 ጀምሮ በወዳጅነት አደባባይ አንፊ ትያትር ይቀርባል ተብሏል።
የትያትሩ መራሔ ተውኔት ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር ) ጸሓፊ ተውኔት ያሬድ ሹመቴ ፣ የሙዚቃ ደራሲው እዩኤል መንግሥቱ መኾናቸው ታውቋል።
እኛ የዓድዋ ልጆች ነን ያለው መራሔ ተውኔቱ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ እንዳሉት ትያትሩ በአዲስ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ዓድዋን በመድረክ ላይ ለዕይታ እንዲቀርብ ማድረግ ዋና ዓላማችን ነው ብለዋል።
ኹላችንም ዓድዋ ለኔ ምንድነው ብለን እንድንጠይቅ በሚያደርግ መልኩ ነው የተዘጋጀ መኾኑን ነው የገለጹት።
ትያትሩ የአንድ ወር ጊዜ እንደወሰደና 350 በላይ ተዋንያን፣ ሙዚቀኞችና ተወዛዋዦች እንደተሳተፉበት ተጠቅሷል።
የትያትሩን የውዝዋዜ ኬሮግራፊ ያዘጋጀው ልጅ ተመስገን መለሰ(ተሙ) ነው።
ኅብር ያለው የባሕላዊ ሙዚቃ መሳሪያ እንደተጠቀሙ የሙዚቃው ደራሲ እዩኤል መንግሥቱ ገልጿል።
በከፍተኛ በጀት የተሠራ ትያትር እንደኾነም ተነግሯል።
ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
