
ባሕር ዳር: የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ምዕራፍ እና በአማራ ሕዝብ የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ መነሻ ናት – ወልቃይት።
“ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” ያሉ ትንታግ የአማራ ወጣቶች እንደ አንድ አንደበት ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾነው ተነሱ።
አነሳሳቸው ላይጨርሱ አልጀመሩም ነበርና በርካቶች ውድ ሕይዎታቸውን እና መተኪያ የሌለውን አካላቸውን ሰጥተው “የኢንተርሃሞይ” አቀንቃኞችን እስከመቀሌ ሸኟቸው።
ወልቃይቶች የዘመናት የነፃነት መሻታቸውን እውን እስኪያደርጉ ድረስም ከቀሪ የአማራ ወንድሞቻቸው ጋር በህቡዕ እና በቡድን ኾነው መስዋእትነት ከፍለዋል።
ከአስከፊው የዘመናት ወረራ ነፃ ከወጡ ከዓመት እድሜ ትንሽ ፈቀቅ ያሉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች “ወልቃይት ኾይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እያሉ ታግለው ነፃ ያወጧቸውን ወንድሞቻቸውን ተዘዋውረው እያመሰገኑ ነው። ትናንት ጎንደር ነበሩ፣ ዛሬ ባሕር ዳር ከትመዋል። በቀጣይም ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ።
በዛሬው የባሕር ዳር ቆይታቸው ስላለፈው ኹሉ በምሥጋና ጀምረው ስለመጪው ደግሞ ተነጋግረው ይቋጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሁናዊ ሁኔታ፣ የአማራ ሕዝብ የቀጣይ የቤት ሥራዎች ምክክር እና ጉብኝት የመርኃ ግብሩ አካል ናቸው ተብሎ ይጠበቃል።
በመርኃግብሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር)፣ ወጣቶች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ከወልቃይት እስከ ባሕር ዳር ያለው የጉብኝት መርኃ ግብር እና የቀጣዮቹ ጉብኝቶች ዓላማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ነው ተብሏል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
