
ደብረ ማርቆስ: የካቲት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ፈንታ መስተሳህል ይባላሉ በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚኖሩ ጥሮተኛ ናቸው። የወጣትነት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለሰላሳ ዓመታት ሀገራቸውን በሙያቸው አገልግለዋል። እኒህ ጥሮተኛ በሙያቸው በወጣትነት ዘመናቸው በዓባይን ጥቅም አልባ ጉዞ የኢትዮጵያውያን የበይ ተመልካችነት ይቆጫቸው እንደነበርም ያስታውሳሉ።
አቶ ፈንታ 2003 ዓ.ም መጋቢት 24 ያ የቁጭት ዘመን ታሪክ ሊሆን ዓባይ ሕዝቦቹን ሊክስ በጉባ በረሃ እጅ ሲሰጥ የዘመናት ቁጭታቸውን የሚወጡበት ጊዜ ስለመድረሱ መገንዘባቸውን የተናገሩት።
በዚያን ጊዜ ነበር ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የተዘረጉት የእኒህ ጥሮተኛ የመስጠት እጆች የግድቡን ፍፃሜ ሳይመለከቱ ላይታጠፉ ቃል ኪዳን ያሰሩት።
ለዚህም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ ወዲህ ለ11 ዓመታት ያለማቋረጥ ከጥሮታ ደመወዛቸው በየወሩ የ1ሺህ ብር ቦንድ በመግዛት በዓባይ ላይ የነበራቸውን ቁጭት እየተወጡ ሲሆን ሀገር ወዳድነታቸውንና ቃል አክባሪነታቸውን በተግባር አሳይተዋል::
አቶ ፈንታ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሪቫን ሳይቆረጥ ቦንድ መግዛት እንደማያቋርጡና ቃላቸውን ጠብቀው እንደሚዘልቁም አረጋግጠዋል።
የትዳር አጋራቸውና ልጆቻቸው የአቶ ፈንታ ሃሳብና ተግባርም ተጋሪ ሲሆኑ የእሳቸው ያልተቋረጠ የቦንድ ግዥ ጤና እና እድሜ ያልገደበው፣ የሀገር ፍቅርና ለቃል መታመን በተግባር የታየበት፣ የዓባይ የዘመናት ቁጭት መልስ ያገኘበት፣ በመሆኑ ቤተሰቡ በእሳቸው ኮርቷል።
ዘጋቢ:–ዘላለም አስፋው–ከደብረ ማርቆስ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
