
ደሴ: የካቲት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሲያትል፣ ዋሽንግተን፣ ኦሪገን፣ አይዳሆ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በደቡብ ወሎ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
ቤተክርስቲያኗ ለተጎዱ ወገኖች የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የምግብ ድጋፍ አድርጋለች። የምግብ ድጋፉንም በአልማ በኩል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እና የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በተገኙበት ድጋፉ ተበርክቷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሲያትል፣ ዋሽንግተን፣ ኦሪገን፣ አይዳሆ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ድጋፉ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል። የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ የኹሉም ዜጋ ኃላፊነት መኾኑን ገልጸዋል።
የአማራ ልማት ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ ሞገስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘርና የቆዳ ቀለም ሳትለይ እያደረገች ያለው ድጋፍ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። ማኅበረሰቡ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈፀመበት ግፍ እና መከራ ከፍተኛ መኾኑን ገልፀው ሌሎች አካላትም ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ቤቴል መኮንን – ከደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
