
ባሕር ዳር: የካቲት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሴቶችን፣ ህጻናታን እና አረጋዊያንን የትኩረት ማዕከሉ ያደረገው የአሸባሪው ሸኔ ጥቃት መሰረቱ ተወልዶ ያደገበት ትህነጋዊ ስሪት እና መንፈስ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግጭቶቹን ሃይማኖታዊ እና ርእዮተ ዓለማዊ ለማድረግ ሲሞክርም ይስተዋላል፡፡
ለሽብር ቡድኑ ሸኔ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ወድቀው እና ተነስተው በገነቧት ሀገር አንዱ ባለሀገር ሌላኛው ደግሞ ባይተዋር አድርጎ መሳልን አሸባሪው ትህነግ የሰጣቸው የዘር መጫዎቻ ካርድ ነው፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት ከዘመናት እረብ አልባ የጫካ ሕይዎት የተመለሱት የትህነግ ፈረሶች መቀሌ ምሳ ተጋብዘው ወለጋ ቢደርሱም ወደለመዱት የጫካ ሕይዎት ለመመለስ ግን ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡
ከነ ትጥቃቸው እና ጫካዊ አስተሳሰባቸው መሐል ሀገር የደረሱት የሽብር ቡድኑ አባላት ሲፈልጉ በሕቡዕ ደስ ሲላቸው ደግሞ በአደባባይ ተጨማሪ ኃይል ሲያሰለጥኑ እና ተደጋጋሚ ጥቃት ሲወስዱ በየደረጃው ካለው የመንግሥት አካል የተሰጠው አጸፋ ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም የሚሉት ብዙ ናቸው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ኦቭ ፕሪቶሪያ እና ኪንግስ ኮሌጅ ሎንዶን የፖለቲካ ሳይንስ ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑትን አቶ አላጋው አባቡን ጦርነት ከሁሉ አስቀድሞ ንጹሃንን ይጎዳል፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት በወለጋ እና አካባቢው እየተፈጸመ ያለው የንጹሃን ግድያም ምንጩ የፖለቲካ ሸፍጥ እና ሽኩቻ ነው ይላሉ፡፡ ።
ሕግ የሚከበረው አንድም በኅይል ካልሆነም ተቀራርቦ በመነጋገር መሆኑንም አቶ አላጋው አስገንዝበዋል።
እንደ አቶ አላጋው እይታ በወለጋ አካባቢ በሽብር ቡድኑ ሸኔ የሚፈጸመው ተደጋጋሚ ግድያ ብሔርን መሰረት ያደረገ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን በኦሮሞ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ፤ ይህ የሚያመላክተው የሽብር ቡድኑ ፖለቲካዊ ተልዕኮ እና ሴራ እንዳለው አመላካች ነው ብለዋል፡፡
መንግሥት በአካባቢው በሚፈጠረው ተደጋጋሚ ጥቃት የማያዳግም መፍትሔ መስጠት ባለመቻሉ አሸባሪ ቡድኑ አሁንም ጥቃቱን ቀጥሎበታል፤ የሽብር ቡድኑ በመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ላይ ተደጋጋሚ እርምጃም ወስዷል ነው ያሉት፡፡
አቶ አላጋው መንግሥት ከአካባቢው የጸጥታ ኀይሎች በተጨማሪ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል መንግሥት ጥምር የጸጥታ ኃይል በማሰማራት ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እንደሚገባውም ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም የተለየ አማራጭ ሃሳብ ያላቸው ኃይሎች ከመንግሥት ጋር ተቀራርበው የሚነጋገሩበት መንገዶችን ማመቻቸት፣ ጥቃት በሚደርስበት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችን ማደራጀት እና በየደረጃው ያለውን የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ማብቃት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
