
ሁመራ: የካቲት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ዓባይ ማደሪያ አጥቶ ግንድ ይዞ ይዞራል” ተብሎ ከሕጻናት እስከ አዋቂ የተዜመለት የሕዝቡን ብሶትና ቁጭት አንግቦ ጎረቤት ሀገርን ሲያጠግብ የነበረው ዓባይ በኢትዮጵያዊያን ኅብር እጆች ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተሳትፎበት ስደቱን ገትቶ ጨለማውን ሊያርቅ ብርሃን መስጠት ጀምሯል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን አፍ ያዘጋ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋገጠ ነው ሲሉ የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ተናግረዋል።
የሁመራ ከተማ ነዋሪ መቶ አለቃ አማረ መኩሪያ “ዓባይ ለእናቱ ብርሃን መስጠት መጀመሩ የዘመናት ቁጭታችንን ገፍፎ በደስታ ያስተቃቀፈን ነው” ብለዋል። በራሳችን ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት የተገነባ በመኾኑም ትልቅ ደስታን ፈጥሮብኛል ነው ያሉት።
“የግድቡ ኃይል ማመንጨት የኢትዮጵያን የልዕልና ከፍታ ያሳየንበት የዓድዋን ድል በልማት የደገምንበት ነው” ያለችን ደግሞ ወጣት ሶስና ግርማ ናት። ወጣት ሶስና ቦንድ በመግዛት የድርሻዋን እንደተወጣች ገልጻለች።
የሁመራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በሪሁን እያሱ የሕዝቦች የአንድነት ዐሻራ ያረፈበት ታላቁ ግድባችን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ከኢትዮጵያ አልፎ ጎረቤት ሀገሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመኾኑ ለሀገራችን አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል።
ዓባይ እስትንፋሳችን ነው ያሉት አቶ በሪሁን ዓባይን ተጠቅመን የሥራ እድል በመፍጠር፣ የኢንዱስትሪ መዳረሻዎችን በማስፋት፣ የተፈጥሮ ሃብትን በማልማት ምጣኔ ሃብትን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያዊያን ተረባርበን ግድቡን እንደጀመርነው እና ለዚህ እንዳደረስነው ኹሉ በአንድነት ልንጨርሰው ይገባል ብለዋል።
ሕዝቡ ዓባይን ለመገደብ ያሳየውን አንድነት የውስጥ ነቀርሳ የኾነውን አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለማጥፋት በጋራ ሊቆም ይገባልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ – ከሁመራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
