ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው ልዩ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል

194

የካቲት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው ልዩ ስብሰባ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ከዚህ በፊት ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የተገኘውን ግብዓት ምክር ቤቱ ከተመለከተ በኋላም መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን እጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረሥላሴ

3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ

4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሐመድ

5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

7. አቶ ዘገየ አስፋው

8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

9. አምባሳደር መሐሙድ ድሪር

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና

11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ እጩ ኮሚሽነር ኾነው ቀርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው ልዩ ስብሰባ በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፋብኮ ዘግቧል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 14/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleምክር ቤቱ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ።