
ከሚሴ: የካቲት 13/2014 ዓ.ም(አሚኮ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በሰላም ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተገልጿል። ለዚህም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነው የውይይቱ ተሳታፊ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተናገሩት። በተለይ ከአጎራባች ዞኖች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ይህንን ለማደናቀፍ የሚጥሩ አካላት አይሳካላቸውም ብለዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ አሊ ሕዝቡ የጥፋት ቡድኖችን በመጠቆም ለሕግ እንዲቀርቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። ከሕዝቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም ገልጸዋል። ለሃይማኖቱና ለባሕሉ ተገዥ የኾነ ማኅበረሰብ ያለ በመኾኑ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በሚንቀሳቀሱበት ኹሉ ስለሰላም እንዲሰብኩም ጠይቀዋል።
በሃይማኖትና በብሔር ሽፋን ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ለመመከት ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው ከአጎራባች ዞኖች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከሰላም ኮሚቴዎች ጋር እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም- ከከሚሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
