የሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ አስተዳደር በመንዝ ጌራ ወረዳ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

279

ደብረ ብርሃን: የካቲት 13/2014 ዓ.ም(አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ አስተዳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የመንዝጌራ ወረዳ ነዋሪዎች ግምቱ ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ብር የሚያወጣ 400 ኩንታል ስንዴ ድጋፍ አድርጓል።

በመንዝ ጌራ ወረዳ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከአርሶ አደሩ ያሰባሰበውን 400 ኩንታል ስንዴ ያስረከቡት የሀገረማርያም ከሰም ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሸጋዉ ጫኔ ናቸው። በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸዉን ወገኖች መደገፍ የኹሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የወረዳው ሕዝብና አስተዳደር የሚያደርገዉን ደጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ድጋፉን የተረከቡት የመንዝ ጌራ ወረዳ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጣልባቸው በቀለ የሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ሕዝብና አስተዳደር ያደረጉት ድጋፍ ለወገን ወገን ደራሽ መኾኑን ያስመሰከረ ነው ብለዋል። ለተደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል።

የሽብር ቡድኑ ከ 35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን የገለጹት አቶ ጣልባቸዉ የሚደረገዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ:- ሀብታሙ ዳኛቸው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በኅልውና ዘመቻው በጀግንነት ለተሰው የዘማች ቤተሰቦችና ጉዳት ለደረሰባቸው ዘማቾች የእውቅና እና የምሥጋና መርኃ ግብር አካሄደ።
Next articleበሃይማኖትና በብሔር ሽፋን ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ለመመከት ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር እንዲሠራ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ አሊ ጥሪ አቀረቡ።