
እንጅባራ: የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሀገር ክብር ሲባል መተኪያ የሌላት ሕይዎታቸውን አሳልፈው ለሰጡ እና አካላቸውን ለገበሩ ጀግኖች ነው ዛሬ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የእውቅናና የምሥጋና መርኃ ግብር ያዘጋጀው።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ እንግዳ ዳኛው ከአስተዳደሩ የተውጣጡ የሚሊሻና የፋኖ አባላት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተቀናጅተው ጠላትን ድባቅ በመምታት አኩሪ ገድል መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
መርኃግብሩ የማይተካ ሕይወታቸውን ገብረው ሀገር ላፀኑ ጀግኖች ባይመጥንም የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሕዝብ እና መንግሥት ከጎናቸው መኾኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም በዘላቂነት የማቋቋም ተግባሩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራ ነው ዋና አስተዳዳሪው የገለጹት።
የዘማች ቤተሰቦችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል። ቤተሰቦቻቸው ለሀገር ነጻነትና ክብር በከፈሉት መስዋእትነት በተገኘው ድልም ኩራት እንደሚሰማቸውም ገልጸዋል፡፡
ዋጋ ተከፍሎበት የተገኘው ድል በዘላቂነት እንዲረጋገጥና ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዲኖሩ መንግሥት ኀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አንስተዋል።
በመርኃግብሩ ከኅልውና ዘመቻው በድል የተመለሱ የፀጥታ አካላት፣ የጤና ባለሙያዎች እና በጦርነቱ በክብር የተሰው የጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች ተገኝተዋል። ለእያንዳንዳቸውም የገንዘብ ድጋፍ እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ዘጋቢ:- ሳሙኤል አማረ – ከእንጅባራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
