በእስራኤል በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

95

ባሕር ዳር: የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም” ማኅበር ጋር በመተባበር ‘ገበታ ለወገን’ በሚል የተዘጋጀው የእራት ግብዣ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በአሸባሪ ቡድኖች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚውል ገንዘብ ማሰባሰብ ተችሏል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በእስራኤል የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት “በእስራኤል የምትኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ፣ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ወዳጆች በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በአሸባሪው ትህነግና በኦነግ ሸኔ ጥቃት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ በማሰባሰብ ለወገኖቻችን እያደረጋችሁት ያለው ድጋፍና ትብብር ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጠው ነው” ብለዋል።

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና ለማስቀረት በተካሄደው በቃ/#no more በሚለው ዘመቻ በእስራኤል ያሉት የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋፅኦም አመስግነዋል።

“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም” ማኅበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሞላ ሚካኤል እኛ በእስራኤል ያለን የዳያስፖራ አባላት ሀገራችን ፈተና በገጠማት ጊዜ በተቻለን አቅም ከጎኗ ልንቆም ይገባል ብለዋል። ይህንም ስናደርግ በትልቅ ፍቅርና ተስፋ በመሆኑ ሁሌም ሀገራችን በምታደርገው ጥሪ የበኩላችንን ለማበርከት ዝግጁ ነን ነው ያሉት። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“እንደጀመርነው ለዚህ አብቅተነዋል፤ በአጭር ጊዜ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ተሟላ ድል እናሸጋግረዋለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።
Next articleየአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በኅልውና ዘመቻው በጀግንነት ለተሰው የዘማች ቤተሰቦችና ጉዳት ለደረሰባቸው ዘማቾች የእውቅና እና የምሥጋና መርኃ ግብር አካሄደ።