
“እንደጀመርነው ለዚህ አብቅተነዋል፤ በአጭር ጊዜ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ተሟላ ድል እናሸጋግረዋለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ለመላ ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
“ለዚህ ታሪክ እውን መኾን ዐሻራችሁን ያሳረፋችሁ ባለሙያዎች፣ ሕዝባዊ ተሳትፎውን ያስተባበራችሁ አካላት፣ በሀገር ቤት እና በውጭ የምትኖሩ መላ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ወደኋላ ያለፈባቸው የታሪክ አንጓዎች ኹሌም በደማቁ እንደሚታወሱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
ግድቡ በኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ድጋፍ እና ተሳትፎ፣ የባለሙያዎች ጥረት እና የአመራር ጥበብ በደረሰበት የግንባታ ደረጃ ተርባይኑ ኃይል ወደ ማመንጨት ተሸጋግሯል ብለዋል።
“እንደጀመርነው ለዚህ አብቅተነዋል፤ በአጭር ጊዜ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ተሟላ ድርብርብ ድል እናሸጋግረዋለን”ነው ያሉት፡፡
የቀደሙ አባቶቻችን ነፃነት ከማውረስ ጀምሮ አኩሪ ታሪክ ሠርተው አልፈዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ትውልድ ዕድለኛ ኾኖ አኩሪ ገድል ፈፅሟል፤ ለመጪው ትውልድም ታሪካዊ መደላድሉን አኑሯል ብለዋል።”እንዲህ አይነት ገናና እና አኩሪ ታሪክ በሚሠራ ሀገር እና ሕዝብ መሐል ሀገር የካዱ ባንዳዎች ንጹሐንን የማጥቃት እና ሀገር የማፍረስ ተልእኮ ውስጥ ተሰማርተው ማየት የእናት ሆድ ዥንጉርጉርነትን በገሃድ የሚያሳይ ነው” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
አንዳንድ ባንዳዎችና ጨካኞች ለጊዜው ብዙ ዋጋ እያስከፈሉ መኾኑን የጠቀሱት አቶ ደመቀ በኹሉም ማዕዘናት ያሉ ኢትዮጵያውያን በየዘመኑ የሚገጥማቸውን ፈተና በድል እየተሻገሩ ወደፊት መትመማቸውን ይቀጥላሉ ነው ያሉት።
“በቀጣይም ለመጪው ትውልድ ትልቅ ዐሻራ በማኖር በኹሉም መስክ ታላቅነታችንን በጋራ እውን ለማድረግ እንድንረባረብ አደራ ለማለት እወዳለሁ!” ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
