
የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉባ ተካሂዷል፡፡
በሥነ ሥርዓቱም የመከላከያ ሚኒስትር እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም በላይ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከኃይል ማመንጨነት ባለፈ ጠንካራ የኢኮኖሚ ስብሕት ማእከል መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት መኾኑን አንስተዋል፡፡
ዶክተር አብርሃም እንዳሉት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አኹን ለደረሰበት ስኬት ያለፉት መሪዎች ሕልማቸውን ያንጸባረቁበት ታላቅ ሕልም ውጤት ነው፡፡ ይህ ትውልድም ከጊዜ ጋር የታረቀ የመሪዎቹን ሕልም ያሳካ ትውልድ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የሙያ ሽግግር እንዲኖር ያስቻለ እንደኾነ ጠቅሰዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ውስብስብ የሲቪል፣ የኤሌክትሪክ እና ሜካኒካል ምሕንድስና ሥራዎችም የተከናወኑበት በመኾኑ ለሙያው ዘርፍ ዕድገት ትልቅ አቅም መኾኑን አንስተዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ፕሮጀክቱ በርካታ የአፈጻጸም ችግሮች እንደነበሩበት ያነሱት ዶክተር አብርሃም እነዚህን ችግሮች በብስለት በማስተካከል ለዛሬው የመጀመሪያ ኃይል ማመንጫት ምዕራፍ መድረስ መቻሉንም ነው ያነሱት፡፡
ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ከማሟላት ባለፈ በሀገሪቱ በየዓመቱ እየጨመረ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ወደ ሥራ ሲገባም ከሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን ለማግኘት ከፍተኛ ድረሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ግድቡ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ በአካባቢ ጥበቃ፣ በቱሪዝም ልማት እንዲሁም ሌሎች ግዙፍ ሥራዎችን በማከናዎን ጠንካራ የኢኮኖሚ ስብሕት ማእከል መፍጠር የሚያስችል መኾኑን አስገንዝበዋል፡፡
ግድቡ በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሚያግዙ ሥራዎች እየተከናወኑ በመኾኑ ኢትዮጰያውያን በአንድነት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
