
የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገራት ቀጣናዊ ምጣኔ ሃብታዊ ውህደትን ለማፋጠን ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።
አቶ ደመቀ በ58ኛው የሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።
አቶ ደመቀ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀጣናው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ቡድኖችን ለማክሰም የሚያስችል ጠንካራ ድጋፍ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክን የማጠናከር አስፈላጊነትንም አንስተዋል።
የኹሉንም የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሀገራት ጥቅሞች ሊያስከብር የሚችል የጋራ የትብብር ማዕቀፍ መመስረት እንደሚገባም ነው የገለጹት። እ.ኤ.አ በ2019 ኢትዮጵያን ባገለለ ሁኔታ የቀይ ባሕር ሀገራት ፎረም መቋቋሙ ስህተት መኾኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ለአካባቢው ካላት ቅርበት አኳያ በቀይ ባሕር አካባቢ የሚመሰረት ማንኛውም የሀገራት የጋራ ጥምረት ኢትዮጵያን ማካተቱ ምክንያታዊ ነው ብለዋል።
በቀይ ባሕር አካባቢ የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን እንዲሁም ሕገ-ወጥ የስደተኞች ዝውውርን ለመግታት በባለብዙ ወገን መድረክ ደረጃ የተጠናከረ የጋራ ትብብር ማድረግ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በማቀድ ለምታካሂደው ሀገራዊ ምክክር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገቢውን እውቅና እንዲሰጥ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል።
የሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሙስናን መከላከል፣ የእውቀት ሽግግርን ማበረታታት እንዲሁም የዓለም ሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሦስት ቀናት የሚካሄድ መኾኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
