እነሆ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የዓባይን ፍሬ ለመቋደስ በቃን።

169

የካቲት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሐሳቡ መወጠን ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ልዩ ልዩ መሰናክሎችን ፈጥረዋል። ኹሉም ኢትዮጵያውያን ዐሻራቸውን ባሳረፉበት በዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት የተነሳ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ከምጣኔ ሀብታዊ አሻጥር እስከ ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለማድረስ ሞክረዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ግድቡ ከፍተኛ ችግሮች ተስተውለውበት ነበር። በስድስት ዓመታት ይጠናቀቃል የተባለው ይህ ፕሮጀክት 10 ዓመታትን እንዲሻገር ኾኗል።

ከመጋቢት 2010 መንግሥታዊ ለውጥ በኋላ ሀገራዊ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ነው። የደረሰበት ችግር በጥናት ተለይቶ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ተግባራዊ ሥራ ተጀመረ። በዚህ ርምጃ መሠረት በፍጥነት መገንባት ተጀመረ። በ2012 እና 2013 ዓ.ም አንደኛው እና ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌትም በስኬት ተጠናቀቀ። እነሆ ዛሬ ደግሞ እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ኹለት ተርባይኖች ከዛሬ ጀምሮ ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ። ይህም የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻል ጀምሮ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትሩፋት ብዙ ነው።

ይህ ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ጫናን የሰበረ በአፍሪካ የዘመኑ ትልቅ ታሪካዊ ድል ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

የኢትዮጵያውያን የይቻላል መንፈስ የታየበት የሕዳሴ ግድቡ የመጀመሪያ ኀይል ማመንጨት ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዓለም ይበሰራል።

ግድቡ 145 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል። 1 ነጥብ 78 ኪሎሜትር ገደማ ርዝማኔ አለው። በግድቡ ግራና ቀኝ የሚገኙ የኃይል ማመንጫዎች እያንዳንዱ 13 ተርባይኖች አሉት።

ግድቡ ሲጠናቀቅ በ 240 ኪሎሜትር ሐይቅ በመፍጠር 74 ቢሊዮን ሜትር ኩዩብ ውኃ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም የአካባቢውን ሥነምህዳር ከመለወጥ አንስቶ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው እምርታ ከፍተኛ ነው።

በደጀኔ በቀለ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleሰበር ዜና : ዓባይ ብርሃን መስጠት ጀመረ።
Next article“ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአፍሪካ ቀንድ ጽንፈኝነትን ለማክሰም የሚያስችል ጠንካራ ድጋፍ ሊሰጥ ይገባል”ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን