
ደሴ: የካቲት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ምሁራን መማክርት አዘጋጅነት ጉባኤ አማራ ሦስት በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው የምክክር መድረኩ ዓላማዎች የአማራን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን መለየት፣ በክልሉ ውስጣዊና ውጫዊ የሰላምና ደኅንነት ስጋቶች ላይ በጥልቀት መወያየት፣ የመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ላይ ወጥ የሆነ የጽንሰ ሀሳብ አረዳድ እና ተጓዳኝ የሆኑ ኀላፊነቶችን በመለየት የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ሊካሄድ በታሰበው ሀገራዊ የምክክር መድረክ የአማራ ሕዝብ ሊኖረው ስለሚገባ ተሳትፎ እና አማራን በመወከል የሚሳተፉ አካላት ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ ዝግጅቶች የጋራ ግንዛቤ እና አቋም መፍጠር እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ሚና መጠቆም እና የተግባር አቅጣጫ ማስቀመጥ ጉባኤው የሚመክርበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በየትኛውም መመዘኛ ውጤታማ ሥራ ለማከናወንና የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ጠንካራ መግባባት፤ ወጥ የሆነ አቋም እና ሁሉንም የሚያግባባ የጋራ ጥያቄ ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡
እነዚህን ጥያቄዎች እና ዓላማዎች መልክና ቅርጽ አስይዞ በመደገፍ ሥርዓትና ስልት ማበጀት የሚችሉት ደግሞ ምሁራን መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡
መላው የአማራ ሕዝብ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር እንደሚገባውም ርእሰ መስተዳድሩ
አሳስበዋል፡፡
ውስጣዊ አንድነትንና ሰላምን ማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድግ በመረዳት የአማራ ሕዝብ በዚህ አቋም እንዲግባባ ለማድረግ የምሁራን እና የማኅበራዊ አንቂዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ:–ሀያት መኮነን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
