
ባሕር ዳር: የካቲት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቤልጂየም ብራስልስ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የአውሮፓ ህብረት እና አፍሪካ ህብረት የጋራ ጉባኤ ለመሳተፍ ነበር ወደ ብራሰልስ ያቀኑት።
ጉባኤው ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በነበረው ቆይታ በሁለቱ ወገኖች ባለው ትብብር ዙሪያ በጥልቀት መክሯል።
የጋራ እና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ 150 ቢሊዮን ዩሮ የአፍሪካ-አውሮፓ የኢንቨስትመንት እቅድ ይፋ ተደርጓል።
ይህም የትምህርትና የጤና ዘርፍን ያካተተ ሲሆን የአውሮፓ-አፍሪካ የ2030 የጋራ ራዕይን እና አጀንዳ 2063ን ለማሳካት እንደሚያስችልም ነው የተመለከተው።
በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው በርካታ ሀሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና የአጋርነት ሁኔታ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የአፍሪካ ድምጽ ስለሚሰማበት እንዲሁም የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል የተመለከቱ ጉዳዮች ተቀባይነት አግኝቷል።
እንደዚሁም የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ጉባኤ ላይ አንስታለች። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
