126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገለጸ።

120

የካቲት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ)126ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ ለኢትዮጵያዊያን ሕብረት የአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ መልዕክት እንደሚከበር የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ፥ በዓድዋ ጦርነት የጣሊያን ጦር ድባቅ ተመቶና ሽንፈትን ተከናንቦ የተመለሰበት መኾኑን አውስተዋል። ድሉ ለአፍሪካዊያንም ትልቅ ድል መኾኑን አስታውሰዋል፡፡

በዓሉ ከየካቲት 15 – 23/2014 ዓ.ም በኪነ ጥበብ ዝግጅቶች፣ ፓናል ውይይት፣ በኹሉም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ሚሲዮኖች የተለያዩ ዝግጅቶች አውደ ርዕይ እና ዓውደ ጥናት ይከበራል። በኹሉም ክልሎችና ከተማ መሥተዳድሮችም በተለያየ ደረጃ የሚከበር መኾኑንም አብራርተዋል።

ኹሉንም ተግባራት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በድምቀት እንደሚከበር መገለፁንም ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የካቲት 12 እኛ ኢትዮጵያዊያን በጠላት ስንነካና ስንጠቃ ይበልጥ የምንጠናከርና የምንሰባሰብ ስለመኾናችን ምስክር ነው!” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብራሰልስ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ።