❝የቀደሙት አያቶቻችን በመስዋእትነት ነፃነቷን ጠብቀው ያቆዩልንን ሀገር ከነክብሯና ነፃነቷ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ግዴታ አለብን❞ ዶክተር ሂሩት ካሳው

167

የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዓድዋ ድል ኢትዮጵያኖች ፋሺስት ኢጣሊያን ድል ሲያደርጉ በዓለም ሕዝብ ዘንድ ግርምትን ሲፈጥር የጥቁሮችን ድል አድራጊነት ያበሰረ አዲስ ታሪክ ነጋሪ ነበር።

በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ በወቅቱ ኢትዮጵያዊያን አርበኞችና ወጣቶች ለሀገራቸው ሲሉ ተፋልመው በጀግንነት መስዋእትነት በመክፈል ለአሸናፊነት በቅተዋል።

የካቲት 12/1929 ዓ.ም በጦር አዛዥ ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ቦንብ በመወርወር በጠላት ላይ ጥቃት የፈፀሙት ወጣቶች አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወጣቶቹን እርምጃ ተከትሎ የፋሽስት ኢጣሊያ ሠራዊት በሦስት ቀናት ብቻ በአዲስ አበባ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውንን መጨፍጨፉም ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተገናኘ የፋሽስቱን የጭካኔ ድርጊት ለማስታወስ በየዓመቱ የካቲት 12 የኢትዮጵያን ጀግኖች ሰማእታት በመኾን ይዘከራል። ዕለቱ ለኢትዮጵያ ነፃነት ሲሉ ከወራሪ ኃይል ጋር የተፋለሙና የተዋደቁ ጀግኖችን የሚያስታውስ መኾኑም ይታወቃል።

ነገ የሚዘከረውን 85ኛ ዓመት የየካቲት 12 የሰማእታት ቀን መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም የቀደሙት አያቶቻችን በመስዋእትነት ነፃነቷን ጠብቀው ያቆዩልንን ሀገር ከነክብሯና ነፃነቷ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ግዴታ አለብን ሲሉ የአዲስ አበባ ባሕል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት፣ በፍቅርና በሰላም ተባብረን በመቆም ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለሀገር ግንባታ የምናውልበት ጊዜው አኹን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አባቶቻችን በጋራ ኾነው ያስመዘገቡትን ድል እያከበርን የአኹኑ ትውልድም ከልዩነት ይልቅ አብሮነትና አንድነት የሚጠቅም በመኾኑ በጋራ ኾነን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማሻገር አለብን ብለዋል።

የጥንታዊ ጀግኞች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የአሁኑ ትውልድ በጀግንነት፣ በፍቅርና አንድነት የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ አለበት ነው ያሉት።

የኢትዮጵያን ታሪክ በቅጡ በማወቅና በመረዳት እሴቷን ማስጠበቅ ታሪኳን ማቆየትም የአኹኑ ትውልድ አደራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የጥንታዊ ጀግኞች አርበኞች ማኅበር አባላት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሀገር አንድነት ላይ የደቀነውን የኅልውና አደጋ ወጣቱ በመቀልበስ ታሪክ መሥራቱን ጠቁመው አኹንም የሀገር ፍቅርን የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleከትኬት ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ለወደሙ መሠረተ ልማቶች ግንባታ እንደሚውል የተገለጸው “አቅሌማ” ፊልም ለምረቃ በቃ።
Next articleʺየንፁሐን ደም በግፍ ፈሰሰ፣ ከተማዋ በዋይታ ተመላች”