
የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን አድርሷል።
አሸባሪ ቡድኑ በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳት የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት(ዩኤንዲፒ) ዋና ኃላፊ ቱርሃን ሳልህና ሌሎች የልማት ድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል። አሸባሪው ቡድን በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን ሌሎች መሪዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን ለልዑካን ቡድኑ እንደገለጹት አሸባሪው ቡድን እስካሁን በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ በርካታ ንጹሐን ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል። ተቋማት ለኀብረተሰቡ መስጠት በሚገባቸው አገልግሎት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አመላክተዋል።
አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም ተደጋግፎ መሥራት አስፈላጊ መኾኑን ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው የድርጅቱ ኃላፊዎች የደረሰውን ጉዳት በአካል ተገኝተው በመመልከት ለቀጣይ ድጋፍ ያላቸውን አጋርነት በመግለጻቸው አመስግነዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት(ዩኤንዲፒ) ዋና ኃላፊ ቱርሃን ሳልህ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የቀረበላቸው ገለጻ በአግባቡ የተደራጀና እውነታውን ገላጭ ስለመኾኑ ተናግረዋል።
የተቋረጡ የመንግሥት አገልግሎቶች እንዲጀምሩ፣ በዋናነት በሴቶች ተሳትፎ የሚንቀሳቀሱ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መልሰው እንዲቋቋሙ የማድረግ እንዲሁም ለደረሰው ጉዳት በበቂ ጥናት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ድርጅታቸው እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ልዑካን ቡድኑ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የወሎ ዩኒቨርሲቲን ተዘዋውሮም መመልከቱን ከደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
