
የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኝቷል፡፡
ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ለረጅም ዓመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያላት ናት፡፡ የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መኾኑ ተመልክቷል፡፡
የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ “የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን የሚኮሩበትን ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ ባሕር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ኹሉአቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል በሰው ኃይል ለማደራጀት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን ለሩሲያ ልዑካን ቡድን ገልፀዋል፡፡
ከሌሎች ሀገሮች የባሕር ኃይሎች አደረጃጀትና ቀደም ሲል የነበረውን ልምድ በመውሰድ ሀገራዊ ተልዕኮን በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ተሠርቶ ወደ ሥራ መገባቱን እንደገለጹ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ ከባሕር ኃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
