“በአፍሪካ እና አውሮፓ ሕብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው ሐሳቦች ተቀባይነት አግኝተዋል” አምባሳደር ሂሩት ዘመነ

177

የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በ6ኛው በአፍሪካ እና አውሮፓ ሕብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው በርካታ ሐሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግና በአውሮፓ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛና አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የኹለትዮሽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን አምባሳደሯ ገልጸዋል፡፡
በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና የአጋርነት ሁኔታ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የአፍሪካ ድምጽ ስለሚሰማበት እንዲሁም የወቅቱን የአፍሪካ ሕብረት መሪ ቃል የተመለከቱ ጉዳዮች ተቀባይነት እንዳገኙ ጠቁመዋል።
የአፍሪካና የአውሮፓ ሕብረት ግንኙነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲኾን ኢትዮጵያ ማንሳቷን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ ሀገሮች መሪዎች ጋር በነበራቸው የጎንዮሽ ውይይት በኢትዮጵያና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር ስለሚኖርበት ሁኔታ ምክክር መደረጉን ጠቅሰዋል።
በዚህም ለስድስት ወር የአውሮፓ ሕብረት ሊቀመንበር ከነበረችው ስሎቬኒያ እና አሁን ሊቀመንበርነቱን ከተረከበችው ፈረንሳይ መሪዎች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መወያየታቸውን አስታውሰዋል።
በጉባኤው የአፍሪካ ድምጽ በሰላምና ጸጥታ፣ ድህነትን በመዋጋት፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመቀነስ፣ የታዳሽ ኃይል ልማትን በማጠናከር እንዲሁም በስደተኞች ጉዳይ የአህጉሩንና የኢትዮጵያን መብት ባስጠበቀ መልኩ ተነስቶ የጋራ መግባባት እንደተደረገበት አምባሳደር ሂሩት አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ መጠናከር ለቀጣናው መጠናከር ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ፤ በችግር ውስጥ ኾና የልማት ትልሟን ለማሳካት እየሠራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
በመስኖ ልማት፣ በበጋ የስንዴ ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአረንጓዴ ልማትና በመሳሰሉት ሰፊ ርብርብ እያደረገች የምትገኘው ኢትዮጵያ እውነቷን ለማስረዳት መቻሏን ጠቁመዋል።
በተለይም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አጋጥሞ የነበረው ጦርነት ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበት መኾኑን ማስገንዘብ መቻሉን ተናግረዋል። የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ በአግባቡ መረዳት እንዳለባቸው ለበርካታ ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካል ተገኝተው ያደረጉት ምክክር አጥጋቢ እንደነበር አምባሳደር ሂሩት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article62 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደሴ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አጋጠመው።
Next article“የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን የሚኮሩበትን ጠንካራ ተቋም ለሐገንባት እየተሠራ መኾኑን ተገንዝቤያለሁ” ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ