ኢትዮጵያና ኬንያ ያላቸውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዘርፍ መድገም እንደሚያስፈልግ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጹ።

193

የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያና ኬንያ ያላቸውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዘርፍ መድገም እንደሚያስፈልግ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር መለስ በኬንያ የንግድ፣ የኢንዱስትሪና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳሙኤል ማቶንዳ ከተመራው የኬንያ የቢዝነስ የልዑካን ቡድን ጋር በኹለቱ ሀገራት መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ምክክር አድርገዋል፡፡
በንግድና የዘርፍ ማኅበራት መካከል አጋርነትን ለማጎልበት፣ በንግድ ልዑካን ልውውጥ ኹለቱም ሀገራት ተጠቃሚ የሚኾኑባቸውን አዳዲስ አሠራሮች መተግበር በሚቻልባቸው ጉዳዮችን ከልዑካን ቡድን ጋር ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል።
ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የኢትዮጵያና የኬንያ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በኢኮኖሚው ዘርፍ መደገም እንደሚገባው ጠቅሰው፣ ይህን እውን ለማድረግም በአጋርነት መንፈስ በጋራ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
የኬንያ የንግድ፣ኢንዱስትርና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳሙኤል ማቶንዳ በበኩላቸው የላሙ ኮሪደር ፕሮጀክትና የሞያሌ የመተላለፊያ መስመር ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ የኹለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ኬንያ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ የጋራ የንግድ ምክር ቤት መመስረት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleትውልዱ የነፃነትን ዋጋ ከጀግኖች አባቶች ተጋድሎ መማር እንዳለበት የማኅበራዊ ሳይንስና የታሪክ መምህሩ ተናገሩ።
Next article62 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደሴ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አጋጠመው።