
ደብረ ብርሃን: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሲያትል ዋሽንግተን፣ ኦሪገን ፣ አይዳሆ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት እና ኢትዮ ፓስፊክ ማኅበር በጋራ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዉ ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ዱቄት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሲያትል፣ ዋሽንግተን፣ ኦሪገን፣ አይዳሆ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ድጋፋን ባስረከቡበት ወቅት እንደገልጹት የተፈናቀሉ ወገኖችን መደገፍ የሁሉም ዜጋ ኅላፊነት ነዉ ብለዋል።
ድጋፉን ለተፈናቀሉ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ የማስተባበር ሥራውን የሰሜን ሸዋ ዞን አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እንደሚከውን ተገልጿል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደረጀ ፍቅሬ ያጋጠመንን አሁናዊ ችግር ተባብረን በመስራት እንወጠዋለን ብለዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አካሉ ወንድሙ ቤተክርስቲያኗ እያደረገች ያለዉ ድጋፍ የሚያስመሰግን ነዉ ብለዋል።
ተፈናቃዮችም ለተደረገላቸዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ሀብታሙ ዳኛቸዉ-ከደብረብርሃን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/