
ወልድያ: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ)ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸውና በኅልውና ዘመቻው አገልግሎት ሲሰጡ ለቆዩ የጤና ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከፈጸመው የሰብዓዊ ጉዳት ባለፈ በማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ያደረሰውን ውድመትና ዘረፋ እንረዳለን ያሉት የአክሲዮን ማኅበሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሽያጭ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ወይፈን ማኅበሩ ለደሴ፣ ደላንታ፣ ወልድያ እና ደብረ ብርሃን ሆስፒታል አንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
ማኅበሩ ለጤና ተቋማት ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መኾኑንም ለወልድያ ሆስፒታል የተዘጋጀውን ድጋፍ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል።
የወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጠ ቢገኝም በደረሰበት ዘረፋና ውድመት ለታካሚዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በጎ አድራጊዎች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ የኋላ ጥሪ አቅርበዋል።
ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
አሸባሪው ቡድን ከ236 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዘረፋና ውድመት በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ አድርሷል።
ዘጋቢ:- ካሳሁን ኃይለሚካኤል -ከወልድያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/