“ከሞቀ ጎጇችን ተፈናቅለን ለከፍተኛ ችግር እየተዳረግን ነው” ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች

163

ደብረ ብርሃን: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዜጎች ተወልደው ባደጉበት፣ ዘርተው ባመረቱበት፣ አሽተው በቃሙበት፣ ወልደው በሳሙበት ቀዬ የዜጎች የመኖር መብት ባለመከበሩ እየተፈናቀሉ ይገኛሉ። በተለይም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋና ምሥራቅ ወለጋ ዞኖች የሚገኙ የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው ከፍተኛ ግፍና በደል እንደተፈፀመባቸው ተፈናቃይ ወገኖች ተናግረዋል።

ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሀብትና ንብረታቸውን ጥለው የወጡት እነኝህ ወገኖች አሁን ላይ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

አቶ መክብብ ፈለቀና አቶ ገዛኸኝ በለው ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በማንነታቸው ብቻ የጥቃት ዒላማ ውስጥ ገብተው ከኖሩበት ቀዬ በግፍ እንደተፈናቀሉ ለአማራ ሚዲያ ኮርፓሬሽን (አሚኮ) ተናግረዋል።

ከምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በግፍ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ የሚገኙት እነ አቶ መክብብ አሁን ላይ ለችግር መዳረጋቸውን ነው ለአሚኮ የተናገሩት።

“ሸኔ የሚባል የታጠቀ ቡድን አካባቢያችንን ተቆጣጥሮ አማራን እየመረጠ መረሸን ሲጀምር ሕይወታችንን ለማትረፍ በጫካ እየዋልንና እያደርን እዚህ ደርሰናል” ነው ያሉት ሌላኛው ተፈናቃይ አቶ ገዛኸኝ።

“ከሞቀ ጎጇችን ተፈናቅለን ለከፍተኛ ችግር እየተዳረግን ነው” ብለዋል።

በቀጣናው እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አስከፊ እንደሆነም አስረድተዋል።

ከክልሉ ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን የሚመጡ ወገኖች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በደብረ ብርሃን ከተማ ብቻ ከ20 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

የሽብር ቡድኑ ሸኔ እና ጉዳይ አስፈፃሚ ጀሌዎቹ በግፍ ጭፍጨፋ ፈፅመውብናል ያሉት አቶ መክብብ “የሰላም አየር መተንፈስ ብንችልም መጠማት፣ መራብና መታረዝ እየተፈራረቁብን ለችግር ተዳርገናል” ብለዋል።

ዘላቂ መፍትሔ እንሻለን የሚሉት በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉት እነኝህ ወገኖች ሰላሙ ተረጋግቶ ወደቀያችን እንመለሰ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ አላቸው።

ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ወደ ዞኑ የሚገቡ ወገኖች ጉዳይ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበትና የሚመለከተው የበላይ የመንግሥት መዋቅር አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር መጠየቁንም መዘገባችን ይታወሳል።

ዘጋቢ:-ኤልያስ ፈጠነ-ከደብረብርሃን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።
Next articleሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር በጦርነት ጉዳትለደረሰባቸውና በኅልውና ዘመቻው አገልግሎት ሲሰጡ ለቆዩ የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ።