
የወረ ጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት መረጃው እንደደረሰው ገልጾ የተባለው ጉዳት ገና እንዳላረጋገጠ አመልክቷል፡፡
የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ በንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እና የንብረት ዘረፋ እየፈጸመ ይገኛል፡፡
የሽብር ቡድኑ ኦነግ ሸኔ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም በዓባይ ሸለቆ አካባቢ ባሉ ሰባት የገጠር ቀበሌዎች ላይ ትኩረት እንዳደረገ ይናገራሉ፡፡ ነዋሪዎቹ ለወረዳው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ስለጉዳዩ ተደጋጋሚ መረጃ ቢሰጡም የሚሰማቸው እንዳላገኙ ነው የገለጹት፡፡
የሽብር ቡድኑ የዓባይን ኮሪደር (ቀጣና) በመዝጋት እስከ መሐል ሀገር ድረስ ብጥብጥ እና ሁከት ለመክፈት እየተንቀሳቀሰ ስለመኾኑ ማሳያዎች እንዳሉ ያሳወቁት ነዋሪዎቹ ለዓላማው መሳካት እንቅፋት ባላቸው ነዋሪዎች ላይ ብሔር ተኮር ጥቃት እየፈጸመ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ 14 ንጹሐንን መግደሉን እና ዘረፋ መካሄዱንም ገልጸዋል፡፡
በወረ ጃርሶ ወረዳ ጎሃ ጽዮን ከተማ ትናንት ሕዝባዊ ሰልፍ ሲካሄድም ነዋሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ እንዲያረጋጋ ጠይቀዋል፡፡
የወረ ጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ በተለይም ለአሚኮ በስልክ እንደገለጹት በወረዳው የሽብር ቡድኑ እንቅስቃሴ እየሰፋ መምጣቱንና ተጨማሪ የጸጥታ ኀይል እንዲላክላቸው የክልሉን መንግሥት እየጠየቁ መሆኑን ነግረውናል፡፡
በነዋሪዎቹ ጥያቄ መሠረት የሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ጋር ዛሬ ሕዝባዊ ውይይት እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ መረጃው እንደደረሳቸው የተናገሩት ረዳት ኢንስፔክተር ታምሩ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለማግኜት አሰሳ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/