
አዲስ አበባ: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አንዳሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ በአማራ እና አፋር ክልል ምልክታ አድርገዋል፤ በሶማሌ ክልልም የተከሰተውን ድርቅ ተመልክተዋል፤ ድርጅቱ ችግሩን ለመቅርፍ በሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀዋል፡፡
አምባሳደር ዲና በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሱዳን መንግሥት ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የድንበር እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል ብለዋል።
የመተማ ጋላባት መስመር ለዜጎች ክፍት እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሱዳንን መጠየቋን ነው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ያስታወቁት።
አሜሪካ ኤች አር 6600 በሚል በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚደረገው እንቅስቃሴ ልክ እንዳልሆነ ለማስረዳት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ጉዳዮች እየተሻሻሉ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሃሳባቸውን እያቀረቡ እና ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ዘጋቢ፡-አንዱዓለም መናን-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/