አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን ላይ ጭፍጨፋ፣ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር መፈጸሙን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

256

የካቲት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች መጠነ ሰፊ ወረራ በመፈጸም ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርቱ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አባላት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ንጹሐንን በጅምላ ገድለዋል፣ ሕጻናት እና ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን እና የግለሰቦችን ሃብት እና ንብረት ዘርፈዋል ብሏል፡፡ ከተደፈሩት ሕጻናት እና ሴቶች መካከልም አንዳንዶቹ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ናቸው ብሏል፡፡
ጭፍጨፋው በአሸባሪው ትግራይ ወራሪ ቡድን ወታደሮች ኾን ተብሎ የተፈጸመ እና ከጦርነቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላቸው ንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ነበር ያለው ሪፖርቱ ከነሐሴ መጨረሻ እስከ መስከረም መጀመሪያ ድረስ በጭና እና በቆቦ የተፈጸሙ አስከፊ ጭፍጨፋዎችን አንስቷል፡፡ የተፈጸሙት እኩይ ድርጊቶች ብሔር ተኮር ጭፍጨፋ፣ በአካባቢው ተጨማሪ ግጭት እና ትርምስ መፍጠር፣ ጥላቻ እና ስድቦችን ያካተተ መኾኑን ገልጿል፡፡
በቆቦ የነዋሪዎቹ ብሶት፣ የሚታጠቀው ሲበዛ እና አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወታደሮችን በመቃዎማቸው ብቻ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሐን ላይ የሽብር ቡድኑ አባላት ጥቃት ፈጽመዋል ይላል የአምነስቲ ሪፖርት፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወታደሮች በጦርነት ወቅት ኹሉም ተዋጊ ኃይሎች ሊከተሏቸው የሚገቡ መሰረታዊ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን በመተላለፍ እኩይ ድርጊቶችን ፈጽመዋል ሲል የሚከሰው የአምነስቲ ሪፖርት ለዚህም ማሳያዎችንም አቅርቧል፡፡

በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይሎች ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምረው በወረሯቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ጅምላ ጭፍጨፋ፣ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ አስገድዶ መድፈር፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና በግለሰቦች ሃብትና ንብረት ላይ ዘረፋ እንደፈጸሙ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች እየወጡ ነው ብለዋል፡፡
በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚፈጸመው አስገድዶ መድፈር እድሜያቸው እስከ 14 ዓመት በሚደርስ ሕጻናት ላይ እና በሆስፒታል አካባቢዎችም ሳይቀር የተፈጸመ ነው ስትል አረጋግጣለች፡፡
በጭና እና በቆቦ ከጦርነቱ ማክተም በኋላም በርካታ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች እንዳሉባቸው ከነዋሪዎች ተረድቻለሁ ያለው የአምነስቲ ሪፖርት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካባቢዎቹን መልሶ ለመገንባት እና ደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ መረባረብ አለበት ይላል፡፡ እስካሁን በመንግሥት፣ በበጎ አድራጎት ማኅበራት እና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚደረጉ ድጋፎች ቢኖሩም ከደረሰው ጉዳት አንጻር በቂ አይደለም ነው ያለው፡፡
የአምነስቲ ሪፖርት ከቆቦ እስከ ጭና በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር የያዘ፣ በመረጃዎች የተደገፈ እና ማስረጃዎችን ያጣቀሰ ኾኖ በሰብዓዊ መብት ጥሰቱ የተሳተፉ እና ተባባሪ የነበሩ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና የጦርነቱ መሪዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ሲል ያትታል፡፡
በታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበጎንደር ከተማ በውኃ ሥርጭት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል የጀኔሬተር ድጋፍ ተበረከተ።
Next article“በቃ” (#Nomore) ንቅናቄ – የፓን አፍሪካኒዝም ማስፈጸሚያ አንዱ መንገድ