በጎንደር ከተማ በውኃ ሥርጭት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል የጀኔሬተር ድጋፍ ተበረከተ።

101

ጎንደር: የካቲት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጎንደር ከተማ አስተዳደር ለሕዝቡ የሚያቀርበውን የውኃ ሥርጭት ማሻሻል የሚያስችለውን የጀኔሬተር ድጋፍ አገኘ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጀኔሬተር ከረጅ ድርጅቶች በድጋፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
በከተማዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የውኃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ልዩ ልዩ ሥራዎች ቢከናዎኑም ነዋሪዎቿ አሁንም ውኃ ለማግኘት በአማካኝ እስከ 10 ቀናት መቆየት ግድ ኾኖባቸዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜያት እቅድ አዘጋጅቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወርቅነህ አያል አንገብጋቢውን የውኃ ችግር ለመፍታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልል ቢሮዎችና ዩኒሴፍ እውቅና እንዲኖራቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዘመናዊ ጄኔሬተር በድጋፍ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለውኃ ሥርጭቱ መስተጓጎል አንዱ ምክንያት መኾኑን ያነሱት ሥራ አስኪያጁ ጄኔሬተሩ የአንገረብ ግድብን ውኃ ሳይቆራረጥ ማቅረብ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ይህም በጎ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡
የከተማዋን ሕዝብ ቁጥር የሚመጥን ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንዲኖር እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል፡፡ የአንገረብ ግድብን ደለል መጥረግ በመጀመሩ አቅርቦቱ ከአለፈው ዓመት በተሻለ የውኃ አቅርቦት እንደሚኖርም ገልፀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የውኃ ሀብት አነስተኛ በመኾኑ በመስመር ብልሽት ውኃ ሲፈስ አለማሳወቅ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውኃን ለሕንጻ ሥራ፣ ለመስኖ እና ለመኪና ማጠቢያ መጠቀም እንዲሁም መሰል ብክነቶችን ማስተካከል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ:- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ – ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበጎንደር ከተማ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱ ተገለጸ።
Next articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን ላይ ጭፍጨፋ፣ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር መፈጸሙን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።