
ባሕር ዳር: የካቲት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት እንደሚሠሩ የሁለቱ ሀገራት የጸጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቀሴ ለማረጋገጥ በጋራ የሚሰሯቸውን ሥራዎች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያና ኬንያ በጸጥታው ዘርፍ ተባብሮ በመሥራት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአሸባሪው ሸኔ እኩይ ተግባር ለማክሸፍ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።
ኢንስፔክተር ጀነራል ሄላሪ ሙትያምባይ፤ ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር አካባቢዎችን ጸጥታና ሰላም ለመጠበቅ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸው ሥምምነት ላይ ደርሰዋል ብለዋል።
የመረጃ ልውውጦችን በማሳደግና በማሻሻል በአካባቢው ያለውን ሰላም በጋራ እንጠብቃለንም ነው ያሉት።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገሮች አዋሳኝ አካባቢዎች የሸኔን እንዲሁም የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለማስቆም የጋራ ዘመቻ እናደርጋለን ብለዋል።
የጋራ ዘመቻው ወይም ኦፕሬሽን ውጤታማ እንዲሆን ከአንድ ወር ባጠረ ጊዜ ኬንያ ላይ የመግባቢያ ሥምምነት እንፈራረማለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/