
የካቲት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ የካቲት 8/2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገናል፡፡
ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት ተካሂዷል፡፡
በመኾኑም በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ወደፊትም ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን የምንሠራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የካቲት 08/2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/