“ኹሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ሀገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል” የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ

401

ደሴ: የካቲት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዬች ልክ እንዳለፈው ጊዜ ኹሉ ለሀገራቸው በአንድነት ዱዓ (ጸሎት) ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች እና ሰውነት ይቀድማል በጎ አድራጎት ማኅበር ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ በሀገራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያካሄዱ ነው።

በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ኡለሞች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዳሉት አንድነት እና ሰላምን በጋራ ማስጠበቅ ይገባል። ወሎ የእምነት አባቶች እና የኡለሞች መፍለቂያ መኾኗን ያወሱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ በተለይ በዚህ ወቅት መደጋገፍ እና መተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።

❝ኹሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ሀገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል❞ ነው ያሉት።

የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዬች ለዘመናት አብረው በአንድነት እና በመተባበር የኖሩ መኾኑን ያወሱት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የኹሉም ሃይማኖት ተከታዬች ለሀገራቸው ዱዓ (ጸሎት) እንዲያደረጉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የዳዓዋ እና የፈተዋ ዘርፍ ኃላፊ ሽህ አህመድ አወል በምክክሩ ወቅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች ከአራት ሚሊዬን ብር በላይ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

ዘጋቢ:- አንዋር አባቢ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዜና መጽሔት ባሕርዳር ፡ የካቲት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የተሰጠ መግለጫ