የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!!

380

አመሻሹን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መፈንቅለ መንግሥት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰትና ከእውነት የራቀ መሆኑን እንገልፃለን።
በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነ ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመተባበር መክሸፉን እንገልፃለን።
በመጨረሻም የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን የህዝባችንን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልፃለን።
የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ
የካቲት 8/2014
ጅግጅጋ

Previous articleምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ላይ ይወያያል።
Next articleምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ።