
የካቲት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ በአራት አጀንዳዎች ላይ ከተወያየ በኋላ አጀንዳዎቹ ዛሬ በሚካሄደው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባዔ እንዲቀርብ ወስኗል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጨምሮ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን፣ የግል ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ የውሳኔ ሐሳብን ነው አማካሪ ኮሚቴው በአጀንዳነት የተወያየባቸው።
አማካሪ ኮሚቴው በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጀንዳ አስመልክቶ በስፋት ተወያይቷል። የአዋጁ መነሳት በአዋጁ መደንገግ አጋጥሞ የነበረውን ምጣኔ ሃብታዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ለመፍታት ሚናው የጎላ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ እና የአማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ታገሰ ጫፎ አብራርተዋል።
አዋጁ እንዲነሳ ሲታሰብ የሀገሪቷን የፀጥታ ስጋት ባገናዘበ መልኩ መታየቱንና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሊፈቱ እንደሚችሉ ስለታመነበት መኾኑን አቶ ታገሰ ገልፀዋል።
የአማካሪ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው፣ አሸባሪዎቹ ሕወሓት እና ሸኔ የፀጥታ ስጋት እንደኾኑ ናቸው፤ አዋጁ ከተነሳ ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል ሲሉ ጠይቀዋል።
የፀጥታ ስጋት ባለባቸው የአማራ፣ አፋር ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላና ወለጋ አካባቢዎች መንግሥት የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን አቶ ታገሰ አብራርተዋል።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክተው ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ አፈ-ጉባዔው ጠቁመዋል።
የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው፥ የሀገሪቷ የፀጥታ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን ጠቅሰዋል። ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የተለየ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱም ዛሬ በሚያካሂደው አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ በአዋጆቹ እና የውሳኔ ሐሳቦቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃቸዋል ተብሎ እንደሚጠቅ ከምክር ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/