
ደሴ: የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ካወደማቸውና ከዘረፋቸው ተቋማት መካከል ወሎ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው፡፡ የሸብር ቡድኑ የዘረፈውንና ያወደመውን ሀብት በአጭር ጊዜ መልሶ መገንባት ባይቻልም ዩኒቨርስቲው ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የማኔጅንግ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰለሞን አሊ አሸባሪ ቡድኑ ከፍተኛ ወድመት ቢያስከትልም በእሱ እየቆዘምን ቁጭ ብለን አንጠብቅም ነው ያሉት፡፡ በማኅበረሰቡ በመንግሥትና በግቢው ሠራተኞች ቅንጅት ትምህርት ለማስጀመር መልካም ጅምሮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
በተከናወነው የቅንጅት ሥራም የካቲት 10 እና 11/2014 ዓ.ም አምስት መቶ 4ኛና 5ኛ ዓመት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ለተወሰኑ ቀናት ከቆዩ በኋላ በተለያዩ ፋብሪካዎች ተመድበው የተግባር ልምምድ የሚያደርጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ተማሪዎች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር መላኩ ታመነ (ዶ.ር) በበኩላቸው መልሶ ግንባታው ተግባር በምዕራፍ ተከፋፍሎ እየተተገበረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችሉ ሥራዎች መሠራታቸውን ዶክተር መላኩ ገልጸዋል።
የመልሶ ግንባታውን በዘላቂነት ለማከናወን የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ የመንግሥት አካላትና የአጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ተማሪዎችን በሶስት መንገድ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን የገለጹት ዶክተር መላኩ ከ3ኛ ዓመት በላይ ያሉት ከየካቲት 30 ጀምሮ፣ የ1ኛና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ደግሞ ከመጋቢት 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለመቀበል ጊዜያዊ መርሃ ግብር መያዙን ገጸዋል፡፡
ዘጋቢ:–ደጀን አምባቸው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/