በሰባት ወራት ውስጥ ከ196 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ገለጹ።

149

የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ሰባት ወራት ከሐምሌ 1/2013 ዓ.ም እስከ ጥር 30/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ወራት 196 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ገልጸዋል።

ባለፉት ወራት ከ212 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ 92 ነጥብ 45 በመቶ አፈፃፀም መመዝገቡን ጠቅሰዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ብልጫ ወይም የ16 ነጥብ 20 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 118 ቢሊዮን ብር በላይ የሚኾነው ከሀገር ውስጥ ታክስ ሲሆን ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከ78 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የተሰበሰበው ገቢ በኢትዮጵያ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አራት የገቢዎች ቅርንጫፎች ከሥራ ውጭ ኾነው፣ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና መሰል ተጨማሪ ችግሮች አንፃር ሲታይ የተሻለ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አመላክተዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመረጃና ደኅንነት አመራር የሰለጠኑ የደቡብ ሱዳን የደኅንነት ተቋም አባላትን አስመረቀ።
Next articleበወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በቅርቡ ከአምስት መቶ በላይ የ4ኛና 5ኛ ዓመት ተማሪዎቹን ሊቀበል ነው፡፡