
ባሕር ዳር፡ የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ጋር የ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በፕሮጀክት ስምምነት ፊርማው ላይ ተገኝተው እንደገለጹት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በክልሉ የደረሰው ውድመት ከክልሉም ኾነ ከሀገሪቱ አቅም በላይ ነው። በክልሉ አጠቃላይ ልማት የራሱ የኾነ ተጽእኖ ስለሚኖረው ይህንን በሚመጥንና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መንገድ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ጋር ክልሉ አብሮ እንዲሠራ እድሉ በመፈጠሩ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሃሪ (ዶ.ር) በበኩላቸው የአማራ ክልል እና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎች መስኮች እየተደረገ ላለው ትብብርና አጋርነት አመስግነዋል። በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በክልሉ የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት መልሶ ለማቋቋምና ለመገንባት ሥራዎችን ለማከናወን ከሌሎች ተቋማት በተጨማሪ ዩኤንዲፒ የዚህ መርኃ ግብር አካል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዩኤንዲፒ ኃላፊ ቱርሃን ሳላህ ስምምነቱ በአማራ ክልል ከተፈጠረው ሁኔታ አንጻር መልሶ ለማቋቋም፣ የወደሙትን መሰረተ ልማቶች የመገንባት ሥራዎች ያካተተ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክት ስምምነቱ ለቀጣይ 5 ዓመታት ከክልሉ ጋር አብረን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ነው ብለዋል።
በአካባቢያዊ አሰተዳደርና ሰላም ግንባታ፣ አካታች በኾነ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር እንዲሁም ቀጣይነት ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የፕሮጀክቱ የጋራ ስምምነት ተቀዳሚ ተግባራት እንደኾኑ መግለጻቸውን ከአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/