
ባሕር ዳር: የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በማኅበር ተደራጅተው እና እውቅና ተሰጥቷቸው ለነበሩ ማኅበራት በ2014 ዓ.ም ቦታ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ላለፉት ዓመታት በማኅበር ተደራጅተው እና እውቅና ተሰጠቷቸው ሲጠባበቁ የነበሩት የቤት ማኅበራት በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ የካሳ ክፍያውን እንዲያጠናቅቁ ጠይቋል፡፡ ቀሪዎቹ እውቅና ያገኙ ማኅበራትን ቦታ ለመስጠት በ138 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ የካሳ ግምት እየተሠራ ነው ብሏል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኅላፊ አቶ በትግሉ ተስፋሁን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በመጀመሪያው ዙር 236 ማኅበራት ከእጣ፣ 98 ማኅበራት ከቅደም ተከተል፣ 1 ማኅበር ከመምህራን እና 137 ማኅበራት በአጠቃላይ 472 ማኅበራት ቦታ ይሰጣል ብለዋል፡፡
የቤት መሥሪያ ቦታውን ከሦስተኛ ወገን ነጻ ተደርጎ እየተጠበቀ መሆኑን የገለጹት አቶ በትግሉ 1 ሺህ 276 ተነሽ አርሶ አደሮችን ጨምሮ 11 ሺህ 200 ግለሰቦች በመጀመሪያ ዙር ቦታ ምሪት ቦታ ይሰጣቸዋል ነው ያሉት፡፡
ቀሪ ማኅበራትን ቦታ ለመስጠት 138 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ የካሳ ግምት እንዲሠራለት ለግብርና መምሪያ ተልኳል ያሉት አቶ በትግሉ የካሳ ግምቱ ተጠናቆ እንደመጣ እና ከአርሶ አደሮች ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ እንደተደረሰ የቦታ ሽንሸና ይጀመራል ብለዋል፡፡
በመሸንቲ ሳይት ለተደራጁ ማኅበራት የመምህራን ቦታ በጠያቂ ማኅበራት የካሳ ክፍያ ስላልተከፈለ የቦታ ሽንሸናው እንደሚቆይ የገለጹት አቶ በትግሉ የካሳ ክፍያው በሚመለከተው አካላት ተከፍሎ ከተጠናቀቀ በኋላ የቦታ ምሪቱ እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡ ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ በዝግ አካውንት ማኅበራቱ ካስቀመጡት ብር እንዲታሰብ የቀረበውን ጥያቄ ከተማ አስተዳደሩ ከተቀመጠ መመሪያ ውጭ ስለማይሠራ ማኅበራቱ የተጠየቁትን የካሳ ክፍያ በተቀመጠው ጊዜ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ አቶ በትግሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/