ስዊድን በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያካሄደውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መኾኗን ገለጸች።

280

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሐንስ ሔንሪክ ጋር በወቅታዊ የክልሉ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
በአምባሳደሩ የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ እንደገለጹት ክልሉ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በተከፈተበት የግፍ ጦርነት ሳቢያ የሰብዓዊና የመሰረተ ልማት ጉዳት ደርሶበታል።
ክልሉ አኹን ያለበትን አንፃራዊ ሰላም ተጠቅሞ ወደ መልሶ መቋቋም ልማት ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

የመልሶ መቋቋም ሥራው የበርካታ አጋር አካላትን ድጋፍና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑንም ገለጻ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሐንስ ሔንሪክ የተደረገላቸው ገለጻ ክልሉ የደረሰበት ጉዳት ከባድ እና ዘርፈ ብዙ መሆኑን ለመገንዘብ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
ስዊድንም በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚያካሄደውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሩ መግለጻቸውን ከአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዜና መጽሔት ባሕርዳር ፡ የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 07/2014 ዓ.ም ዕትም